በረመዷን በቀን የፍትወት ፈሳሽን ማውጣት (ማስተርቤሽን)

Home የፈትዋ ገጽ ዒባዳ ጾምና ኢዕቲካፍ በረመዷን በቀን የፍትወት ፈሳሽን ማውጣት (ማስተርቤሽን)

ጥያቄ፡- በረመዷን በቀን ፍትወትን አውቆ ማፍሰስ እንዴት ይታያል?


መልስ፡- ቢስሚላሂር-ረሕማኒር-ረሒም አል-ሐምዱሊል-ላሂ ረብ-ቢል ዓለሚን ወስ-ሶላት ወስ-ሰላም ዐላ ረሱሊላህ

ጥያቄውን እንደሚከተለው እንመልሳለን፡፡

ፍትወትን ለማውጣት ብልትን በእጅ መነካካት የፍትወት ፈሳሽን እስካላወጣ -እንደ ሐነፊዮቹ እይታ- ጾምን አያፈርስም፡፡ በእጁ ሲነካካ ፍትወቱ የፈሰሰ ከሆነ ግን ጾሙ ይፈርሳል፡፡ ነገርግን ሰውየው ቀዷ መክፈል ብቻ ነው ግዴታ የሚሆንበት፡፡

ነገርግን ሰውየው ከዚህ ቆሻሻ ተግባር ሰውየው ራሱን እንዴት ማዳን ይችላል?

ሰውየው ስለወሲብ አብዝቶ እንዳያስብ እንመክረዋለን፡፡ ብዙ ጊዜም ለብቻው እንዳይሆን እንመክረዋለን፡፡ ምንጊዜም ቢሆን ሰይጣን ሲወሰውሰው እና ይህንን ፀያፍ ተግባር እንዲሰራ ሲጎተጉተው በአላህ ይጠበቅ፡፡ ዉዱእ ያድርግ፡፡ ይስገድ፡፡ ኢስቲግፋር ያብዛ፡፡ ዚክርና ቁርአን ማንበብ ያዘውትር፡፡ እንዲህ ሲያደርግ አላህ ተውበት ይሰጠዋል ብለን እንከጅላለን፡፡ ከዚህ ክፉ ልማድም እንዲመለስ ይረዳዋል ብለን ተስፋ እናደርጋለን፡፡

አላሁ አዕለም!