ሶላትን መርሳት እና ቀዷ መክፈል

Home የፈትዋ ገጽ ሰላት ሶላትን መርሳት እና ቀዷ መክፈል

ጥያቄ፡- ሰውየው ፈርድ ሶላትን ሳይሰግድ ረስቶ ከሁለት ቀን በኋላ እንዳልሰገደው ቢያስታውስ ምን ማድረግ ነው ያለበት?


መልስ፡- ቢስሚላሂረሕማኒ-ር-ረሒም ወልሐምዱ ሊላሂ ወስ-ሶ-ላት ወስ-ሰ-ላም ዐላ ረሱሊላህ።

ፊሊስጢን የሚገኘው አል-ቁድስ ዩኒቨርሲቲ የፊቅህና የኡሱሉል ፊቅህ መምህር ዶክተር ሑሳሙዲን ቢን ሙሳ ዒፋና እንዲህ ይላሉ፡-

በመሰረቱ ሙስሊም ግለሰብ ሶላትን በወቅቱ ጠብቆ መስገድ ተገቢው ነው። ምክንያቱም ጥበበኛው አላህ ለሶላት ውስን ወቅት አስቀምጧል። በተመደበው ወቅቱም መገደብ መልካም ነው። አላህ እንዲህ ይላል፡-

إِنَّ الصَّلَاةَ كَانَتْ عَلَى الْمُؤْمِنِينَ كِتَابًا مَّوْقُوتًا

“ሶላት በምእምናን ላይ በጊዜያት የተወሰነች ግዴታ ናትና፡፡” (አን-ኒሳእ 4፤ 103)

አላህ ሶላታቸውን በወቅቱ፣ ማዕዘናቱን እና መስፈርቶቹን ጠብቀው የሚሰግዱ እውነተኛ ሙእሚኖችን አሞግሷል። አላህ እንዲህ ይላል፡-

(قَدْ أَفْلَحَ الْمُؤْمِنُونَ) إلى أن قال تعالى (وَالَّذِينَ هُمْ عَلَىٰ صَلَوَاتِهِمْ يُحَافِظُونَ) .

“ምእምናን ፍላጎታቸውን ሁሉ በእርግጥ አገኙ (ዳኑ)፡፡”“እነዚያም እነሱ በስግደቶቻቸው ላይ የሚጠባበቁ የኸኑት (አገኙ)፡፡” (አል-ሙእሚኑን 23፤ 1-9)

ይህ የጠቀስነው ሰውየው እያስታወሰ እና እንቅልፍ ላይ ባልሆነበት ሁኔታ ላይ ሲሆን ነው። ሰውየው ተኝቶ ከሆነ ወይም ከረሳና ሶላት ካመለጠው ኃጢያት የለበትም።

የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ይላሉ፡-

إن الله وضع عن أمتي الخطأ والنسيان وما استكرهوا عليه 

“አላህ ለኡመቴ ስህተትን፣ መርሳትን እና የተገደዱበትን ነገር ይቅር ብሏል።” አል-ሐኪም፣ ዳረቁጥኒይ እና ሌሎችም ዘግበውታል።

ከአቡ ቀታዳ እንደተዘገበው “ሰዎች ሰዎች ከሶላት ስለመተኛታቸው ነብዩን ጠየቁ። እርሳቸውም እንዲህ አሉ፡-

إنه ليس في النوم تفريط وإنما التفريط في اليقظة

“በእንቅልፍ ላይ  ወሰን ማለፍ የለም፤ ወሰን ማለፍ ማለት ነቅቶ ሶላት ያሳለፈ ሰው ላይ ነው።” ነሳኢይ፣ ቲርሙዚይ እና አቡዳዉድ ዘግበውታል።

ሶላት የረሳ ሰው ወይም የተኛ ሰው ቀዷውን በፍጥነት ማውጣት ይጠበቅበታል። ምክንያቱም ካልተከፈለ በማይጠራ እዳ ጫንቃው ተይዟል። የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ይላሉ፡-

فدين الله أحق أن يقضى

“የአላህ እዳ ሊከፈል የሚገባው ዕዳ ነው” ቡኻሪይ ዘግበውታል።

በዚህ መሰረት ጠያቂው ረስቶ ያመለጠውን ሶላት እንዳስታወሰው በፍጥነት ቀዷ ማውጣት አለበት።

من نسي صلاة فليصلها إذا ذكـرها لا كفارة لها إلا ذلك

“ሶላት የረሳ ሰው ሲያስታውሳት ቀዷ ያውጣት፤ ከዚህ ውጪ ሌላ ክፍያ የለበትም።” ቡኻሪይ እና ሙስሊም ዘግበውታል።

የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ይላሉ፡-

إذا رقد أحدكم عن الصلاة أو غفل عنها فليصلها إذا ذكرها ، فإن الله عز وجل يقول (وَأَقِمِ الصَّلَاةَ لِذِكْرِي)

“እያንዳንዳችሁ ተኝታችሁ ሶላት ካመለጣችሁ ወይም ከዘነጋችሁ ያስታወሰ ጊዜ ይስገደው። አላህ እንዲህ ይላል፡- :(ሶላትንም /በእርሷ/ እኔን ለማውሳት ስገድ፡፡” ሙስሊም ዘግበውታል።

ወላሁ አዕለም!